.እንኳን አንድ ቤት አንድ ሀገር በሰላም ለመኖር ፍቅርየግድ ያስፈልጋል፡፡
.ነፍስ የተፈጠረችው አንዴ ነው የምትኖረውም ለዘላለም ነው፡፡
.ከማትወደውም ከማይወድህም ሰው ጋር መኖር ከባድ ነው፡፡
.የማይወደውን የሚገዛ ሰው የሚወደውን ነገር መሸጡ አይቀርም፡፡
.አንድን ንብ በተደጋጋሚ ወደ አበባው የሚጠራት የአበባው ማስታወቂያ ሳይሆን የአበባው መልካም መዓዛው ነው፡፡
.ከነ ድህነትህ የሚወድህ ሰው እንጂ ድህነትህን የሚወድልህ ሰው የለም፡፡
ተዋዶ እንደ መጋባት ተዋውቆ መጋባትም ትልቅ ዋጋ አለው፡፡
ልብ ለሌለው ሰው ልብን መስጠት ትርፉ ህመም ነው፡፡
.ሰው ግቢውን የሚያጥረው ጅብ ፈርቶ ሳይሆን ሰው ፈርቶ ነው፡፡
.ራሱን ያሸነፈ ሰው ከማንም ጋር መኖር ይችላል፡፡
.የሰው ልጅ የወደፊት ስጋቱ ሰው ነው፡፡
.በራስ ማዘን የሚመጣው ራስን ካለማክበር ነው፡፡ ኩሽና የበሰለ ሳሎን ይቀርባል፡፡
.አባዬ የባለቤቴ ፀባይ ካገባኋት በኋላ ተቀያየረብኝ፡
.ልጄ እኔም እናትህን ያወቅኳት ካገባኋት በኋላ ነው፡፡
.እኔና ባለቤቴ ሰው እናስታርቃለን እኛ ግን እየተጣላን
እንኖራለን:አለ ሰውዬው!
ማደግ ባይኖር ኖሮ መወለድ ትርጉም አይኖረውም ነበር!
.ወርቅን ወርቅ ነው ያለው ሰው ነው!
.አጥርቶ የማይሰማ ሰው አጥርቶ መናገር አይችልም!