ሕማማት በመድኃኔዓለም ክርስቶስ የምድር ላይ የመጨረሻ 20 ሰዓታት ቆይታ ላይ የሚያተኩር መጽሐፍ ነው:: መጽሐፉ 19 ጊዜ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ የታተመና ከ80 ሺህ ኮፒ በላይ የተሠራጨ ሲሆን በትግርኛ እና በኦሮሚኛ ተተርጉሞ ታትሞአል:: የእንግሊዝኛው ትርጉምም በኅትመት ላይ ይገኛል::
ደራሲው ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በአጠቃላይ 14 መጻሕፍትን ለአንባቢያን ያደረሰ ሲሆን ክብረ ክህነት ፣ቅዱስ ገብርኤል ፣ ታቦት በሐዲስ ኪዳን ፣ ተግባራዊ ክርስትና ፣ ቃና ዘገሊላ ፣ ሀ ቢ ብ ጊ ጊ ዮ ር ጊ ስ ፣ ከ ሞ ት ባ ሻ ገ ር ፣ አ በ ረ ታ ች
መድኃኒት፣ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ፣የኤፍራጥስ ወንዝ ፣ የብርሃን እናት እና የግዮን ወንዝ የሚሉት መጻሕፍት ከሕማማት ውጪ ያሉት መጻሕፍት ናቸው::