አቡሻክር ማለት ወልደ አብ ክቡር ማለት ሲሆን አብሻክር በዐረብኛ ወልደ አብ ክቡር በግእዝ አቡ አባት ሻክር በአማርኛ የክቡር አባት ልጅ ማለት ነው ሁለትኛ አቡሻክር ማለት አበ ስብሐት ማለት በዐለ አኰቴት የምስጋና አባት የምስጋና ባለቤት አዕኳቲ አመስጋኝ ማለት ነው የተነሣበት ዘመን በ 6750 ዐመተ ዐለም በ1250 ዐመተ ምሕረት እስክንድር በነገሠ በ1569 ዐመት ሲሆን ትሩፋት ሠርቶ ግብር ገብቶ 40 ዘመን ዘግቶ በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተቃኝቶ የዚህን መጽሐፍ ጥልቅና ረቂቅ ምስጢር እግኝቶ ዐለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዐለም ፍጻሜ ያለውን የዘመን ቀመር (አቈጣጠር) ጽፎ ለዐለም ዕውቀቱን ያበረከተ ሊቅ ሲሆን መጽሐፉም በራሱ በደራሲዉና በጸሐፊው ስም አቡሻክርተብሏል ልጅ በአባቱ ስም እንዲጠራ እንዲታወቅ፡፡ ይደልዎ ለዘያነብብ ቅድመ ይዝክር ስሞ ለበዐለ መጽሐፍ ወእምዝ ያንብብ ወይምሀር እንዲል መጽሐፍን ለሚያነብ ሰው ሁሉ አስቀድሞ የመጽሐፉን ባለቤት ስም ጠቅሶ (ጠርቶ) ከዚህ በኋላ ማንበብና ማስተማር ይገባዋል እንዳለ ዮሐንስ አፈወርቅ፡