የሰው ልጅ መሳሳቱና ኃጢኣት መሥራቱ የሚገርም አይደለም፤ ጥፋት የሚሆነው ከስህተቱ ካልተመለሰና በአመፁ የሚቀጥል ከሆነ ነው፡፡
ኃጢአት በሠራህ ቁጥር እጅ አትስጥ፤ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ።
ቀና በልና ተረጋግተህ ለውስጥህ እንዲህ በል፦
የሆነ አነስተኛ ፍልሚያ ተሸነፍኩ እንጂ፣ ዋናውን ጦርነት አልተሸነፍኩም።
እርግጥ ነው ምድር ላይ አነስተኛ ግጭቶችን ልንሸነፍ እንችላለን፤
ቁምነገሩ ዋናውን እና ወሳኙን ግጥሚያ አለመሸነፍ ነው፡፡
ወዳጄ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ፤
ዉዱእ አድርገህ ሁለት ረከዐህ ሰላት በመስገድ እንደገና ራስህን ጠግን፤
በዚያው ኃጢአት በሠራህባቸው ጣቶችህ ኢስቲግፋር አድርግ (ከአላህ ምህረትን ለምን)፤
በዚያው ሐራምን ባየህይባቸው ሁለት ዐይኖችህ ቁርኣን ቅራባቸው።
እወቅ! የተፀፃቾች እንባ፣ አላህ ዘንድ፣ ከአላህ ጋር እንደሚደረግ የታዛዦች ሙናጃ, (ሹከሹከታ/መመሳጠር) ነው፡፡
(አላህ)፣ አንተ ወደርሱ እንድትመለስ ባይፈልግማ ኖሮ፣ ራሱን ‹ገፉር› (መሓሪ) ብሎ ባልጠራ ነበር!
"ገፉር" ነኝ ሲል 'ብታጠፋም ና እምርሃለሁ' ማለቱ ነው።