ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የወጣትነትን ክብደት ስመግስጥ፦ "የወጣትነት ዕድሜ የአውሬነት ጊዜ ነው፡፡ በመኾነም ብዙ ተቆጣጣሪዎች፣ መምህA ርእሳነ መምህራን፣ አገልጋዮችና የግል መምህሪን ያስፈልንታል። እነዚህ ሁሉ ተደርገውለት የአውሬነቱ ጠባይ ከቆመ ደስታ ነው፡፡ የልተ7ራ ፈረስ ወይሞ ስማዳ ያልኾነ የዱር አውሬ ማለት ነው ወጣትነት፡፡ ነገር ግን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከልጅነት አድሜው አንሥቶ ከመልካም ሕግጋት ጋር እንዲጣበቅ ካደረግነው ብዙ ደካም ላይጠይቀን ይችላል፡፡ መልካም የኾነት ልማዶቻቸው እንደ ሕግ ይቆጥራቸውና ጥሩነት የሕይወታቸው መመሪያ ና ሕግ ይኾናል፡፡* በማለት ይገልጻል።