1.“ዋጂብ፡- ግዴታ ማለት ነው፡፡ በኢስላማዊ ፍቺው ሰውየው አንድን ነገር ከተወው የሚቀጣበት፣ ከፈጸመው ግን ምንዳን የሚያገኝበት መሆኑን ያመለክታል፡፡
2.“ሐራም፡- እርም ወይም ክልክል ማለት ነው፡፡ ይህ ሰውየው አንድን ነገር ለአላህ ብሎ ከተወው ምንዳን እንደሚያገኝና ከፈጸመው ግን ሊቀጣበት እንደሚችል የሚያመለክት ነው፡፡
3.“ሱና/ሙስተሐብ፡- ተወዳጅ ማለት ነው፡፡ ሰውየው ነገሩን ከፈጸመው ምንዳን እንደሚያገኝበት ከተወው ግን ቅጣት የማያመጣበት መሆኑንን የሚያመለክት ነው፡፡
4.“መክሩህ፡- የተጠላ፡፡ ይህን ሰውየው አላህን ለመታዘዝ ብሎ ከተወው ምንዳን የሚያስገኝለት ነገርግን ከፈጸመው ቅጣት የማያመጣበት መሆኑን ያሳያል፡፡
5.“ሙባሕ”፡- የተፈቀደ፡፡ ይህ አንድ ነገርን መፈጸሙም ሆነ መተዉ እኩል መሆኑን የሚያመለክት ቃል ነው፡፡