ቅዱሳን መላእክት በነገረ ድኀነት (በክርስትና) ከፍተኛ ሱታፌ ናቸው፡፡ ९१チの የእግዚአብሔር ሰማያውያን ፍጥረቱ ስለተፈጥሮአቸው፣ አገልግሎታቸው፧ ኃይላቸው፧ ቅድስናቸው፥ ሞስጋናቸው፧ አማላጅነታቸው፥ ረዳትነታቸው፣ ወዘተ... በብሉይኪዳን፣ በሐዲስ ኪዳንም ሆነ በአዋልድ መጻሕፍት በብዙ ተጽፎ ይገኛል። ነገር ግን በዘመናችን ብዙ ትኩረት ካልተሰጣቸው ርዕሶች አንዱ "ነገረ መላእክት" ነው እላለሁ፡፡ ይህም ክፍተት ቁጥሩ ጥቂት የማይባል ሰው ስለጉዳዩ የመሰለውን እንዲያስተምር በር ሳይከፍት አልቀረሞ። ፈቃደ እግዚአብሔር ሁኖ እነሆ ይህንን ክፍተት ይሞላል ብዬ የማምንበት መጽሐፍ ተዘጋጀ±ል። መጽሐፋ ስስ ንጹሐን መላእክት እና ተያያዥ ጉዳዮች በከፍተኛ ጥንቃቄና ማስተዋል ከመዘጋጀቱ ባሻገር፥ በየዘመናቱ እየተነሱ ለአማኞች ፈተና ስሆኑ ርዕሶች ኦርቶዶክሳዊ መልስን ይዟል፡፡ ከዚህ በፊት ባዘጋጇቸው መጻሕፍት የልተዳሰሱ ይዘቶች ላይ ትኩረት _ እንደሚያደርጉ የተመለከትናቸው መምህር ዲበ ኲሉ ሰንደቄ፤ ንባብ ከሐተታ፧ ትርጓሜ ከምስጢር፣ ትምህርትንም ከእዝናት (ሞክር) አሰናስለው ይህንን የመሰለ መጽሐፍ ስለጻፋልን እያመሰገንሁ፥ አንብበን እንጠቀምበት ዘንድ በአክብሮት እጋብዛለሁ።